እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ከድንግል ተወልዶ

ከድንግል ተወልዶ

ከድንግል ተወልዶ እኛን ሊቀድስ
ተጠመቀ ኢየሱስ በባህረ ዮርዳኖስ
መጥምቁ ዮሐንስ ምንኛ ታደለ
ከነቢያት ሁሉ ሥልጣኑ ከፍ አለ
ትንቢቱን ሊፈጽም አስቦ ክርስቶስ
ተጠምቆ አዳነን በባህረ ዮርዳኖስ
ምስጢረ ስላሴ ታየ የዚያን ለታ
በምን ይከፈላል የጥምቀት ውለታ
እሳተ መለኮት አምላክን ታቀፍሽ
እኛኑ ለማዳን አስቦ ልጅሽ
እመቤቴ ማርያም ምነኛ ታደልሽ
ከአዳም ልጆች ሁሉ አንቺ ተመረጥሽ
ቸሩ አምላካችን መድኀኔዓለም
ኑ እናመስግነው በአንድነት ሆነን

Download

በDec 09, 2024 ተጭኗል