እንኳን ደህና መጡ
ግባ
ጥምቀተ ባህር
ጥምቀተ ባህር
ጥምቀተ ባህር ዮርዳኖስ ነያ(2)
ሃሌ ሉያ(4)
ጌታችን ሲጠመቅ ባሕር ምን አለች
አልችለውም ብላ ወደኋላ ሸሸች
ብርሃነ መለኮት በወንዙ ሲሞላ
ዮርዳኖስም ሸሸ ቀረ ወደኋላ
አዝ -------------
አብ በመጣ ጊዜ ደመናውን ጭኖ
መንፈስ ቅዱስ ታየ በርግብ አምሳል ሆኖ
ለልጁ ምስክር ሊሰጥ ፈለገና
ቃሉን ተናገረ ሆኖ በደመና
አዝ ----------
ጌታችን ሲጠመቅ በሰላሳ ዓመት
ባሕር ኮበለለች ግዑዟ ፍጥረት
ሰማይ ተከፈተ ሆነልን ፀዓዳ
ከሩቅ መቷልና አብ ታላቅ እንግዳ
አዝ -------------
እልል በይ ዮርዳኖስ የጥምቀት መገኛ
የህይወት መሰላል ድህነታችን ለኛ
ቀላያት አብሕርት ብዙዎች እያሉ
እንደምን ተመረጥሽ ዮርዳኖስ ከሁሉ
Download
በDec 09, 2024 ተጭኗል