እንኳን ደህና መጡ
ግባ
ተናገራ ዕዝራ
ተናገራ ዕዝራ
ተናገራ ዕዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
እዝራ በመሠንቆ እያጫወታት ዳዊት ዘመራ
ሳታውቀው አለፈ ያ መልአከ ሞት '' ''
አዝ....................
ትንቢት ተናገሩ ነቢያት በሙሉ ዳዊት ዘመራ
አምላክ ቀዳማዊ ይወርዳል እያሉ '' ''
አዝ........................
ውኆች ቀለም ሆነው እንጨቶች ብዕር ዳዊት ዘመራ
ቢፅፉት አያልቅም የማርያም ክብር '' ''
አዝ....................
የጠፋውን ሊያድን ወረደ ከላይ ዳዊት ዘመራ
የበጎች እረኛ አምላክ አዶናይ '' ''
አዝ................
ጌታ ተጠመቀ በዮሐንስ እጅ ዳዊት ዘመራ
ወገኖቹን ሁሉ በጥምቀት ሊዋጅ '' ''
አዝ.....................
የብርሃናት ጌታ ቸሩ ፈጣሪያችን ዳዊት ዘመራ
ሃሌ ሃሌ ሉያ እንበል ሁላችን '' ''
አዝ.................
እንዘምር /3/ ሁላችን
ለታላቁ ንጉሥ ለመድኅኒታችን
አዝ.................
እንዘምር /3/ በእልልታ
ለታላቁ ንጉሥ ለሠራዊት ጌታ
Download
በDec 09, 2024 ተጭኗል