እንኳን ደህና መጡ
ግባ
መስቀል ተመርኲዘን
መስቀል ተመርኲዘን
መስቀል ተመርኲዘን ወንጌል ተጫምተን
ሃይማኖትን ሰብከን በክርስቶስ አምነን
ማን ያሸንፈናል እኛ ክርስቲያንን
ክርስቶስ አለልን
ንግሥቲቷ ዕሌኒ በጣም የታደለች
በዕጣን ጢስ ተመርታ መስቀሉን አገኘች
መድኃኒት ስትፈልግ ኪራኮስን ይዛ
መስቀሉን አገኘች የዓለሙን ቤዛ
ንዑ ንወድሶ ለዕፀ መስቀል
የተሸከመውን የአምላክን ቃል
ንዑ ንወድሳ ለማርያም ድንግል
አክሊለ ምእመናን ምክሐ ደናግል
ሙታን ተነሥተው ያመሰገኑት
ዕፀ መስቀሉ ነው የእኛ መድኃኒት
መስቀል ምርኲዛችን ጎዳና ወንጌል
ወደ ገነት እንጂ አንሄድም ሲኦል
Download
በSep 21, 2024 ተጭኗል