እንኳን ደህና መጡ
ግባ
ልቦናዬ ያውጣ
ልቦናዬ ያውጣ
ልቦናዬ ያውጣ ውዳሴ ለክብርሽ
ሰላም ለኪ ድንግል ፀጋን የሞላብሽ
የእግዚአብሔር ከተማ የመለኮት ሃገር
ስላንቺ የሚነገር አለን ድንቅ ነገር/2/
አዝ-----
የነቢያት ድንግል የአበው ምሳሌ
እናቴ እልሻለሁ ቢበዛም በደሌ
ከቅዱሳን ሁሉ ያንቺ ክብር ይበልጣል
አምላክን ልጄ ነው ማንስ ብሎት ያውቃል
አዝ-----
ሄዋን ባትታዘዝ ለእግዚአብሔር ቃል
ሞትና መርገሙ ወደ ዓለም ገብቷል
የመላኩን ብስራት በእምነት ብትሰሚ
ሞገስን ተቀበልሽ በቀኙ እንድትቆሚ
አዝ-----
ፍቅርሽ ጉልበት አለው ባህሩን ያሻግራል
ልመናሽ ፅኑ ነው ግዳጅ ይፈፅማል
ስለዚህ ድንግል ሆይ እንወድሻለን
ስምሽን ለልጅ ልጅ እንዘክራለን
አዝ-----
ቀድሞም አልነበረም ወደፊትም አይኖር
ከፍጥረታት ሁሉ በሰማይ በምድር
ከእግዚአብሔር በታች ዛሬም ተሞሽራ
ድንግል ትታያለች ከከበሩት ከብራ
Download
በSep 21, 2024 ተጭኗል