እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ቸሪቱ አማላጂቱ

ቸሪቱ አማላጂቱ

ቸሪቱ አማላጂቱ ሆይ
እናቱ ነሽና ለአዶናይ
በስላሴ ፊት ስልጣን ያለሽ
የባህሪያችን መመኪያ ነሽ (2)
ተጥሎ አዝኖ የኖረው
በልጅሽ ነው ቀናቀና ያለው
ንጉሱን ስትወልጂ በበረት
ተፈታ አዳም ከእስራት
ዘፀውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ (2)
ቸሪቱ አማላጂቱ ሆይ
እናቱ ነሽና ለአዶናይ
በስላሴ ፊት ስልጣን ያለሽ
የባህሪያችን መመኪያ ነሽ
ከሚያስብ ከማይዘነጋ
ፍጥረቱን ከሚያረጋጋ
ስላለሽ በእግዚያብሔር ቀኝ
ለኃጣን ድንግል ለምኝ
ዘፀውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ
ቸሪቱ አማላጂቱ ሆይ
እናቱ ነሽና ለአዶናይ
በስላሴ ፊት ስልጣን ያለሽ
የባህሪያችን መመኪያ ነሽ (2)
ከሰማይ ሰማያት ወርዶ
መለኮት ስጋን ተዋህዶ
አየነው በጠባብ ደረት
ወሰንሽው በአጭር ቁመት
ዘፀውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ
ቸሪቱ አማላጂቱ ሆይ
እናቱ ነሽና ለአዶናይ
በስላሴ ፊት ስልጣን ያለሽ
የባህሪያችን መመኪያ ነሽ (2)
ሰነድ ነሽ መታረቂያችን
ከተማ መማፀኛችን
በሰማይ በምድርም ያሉ
ለክብርሽ ቅኔ ይቀኛሉ
ዘፀውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ
ቸሪቱ አማላጂቱ ሆይ
እናቱ ነሽና ለአዶናይ
በስላሴ ፊት ስልጣን ያለሽ
የባህሪያችን መመኪያ ነሽ (2)

Download

በSep 21, 2024 ተጭኗል