እንኳን ደህና መጡ
ግባ
ሞገድ ሲመታኝ
ሞገድ ሲመታኝ
ሞገድ ሲመታኝ
ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ
ማን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ
በሰላም አለፍኩ በጸጥታ
ሁሉ ተችሎ ለአንተ ጌታ።
በአንተ ቁስል ተፈውስኩኝ
ጌታ በፍቅርህ ተማረኩኝ
ሞቴን ሽረኸው ባንተ ሞት
ይኸው አቆምከኝ በሕይወት።
ደጅ ስጠና ስማጸንህ
መቼ ጨከነ ጌታ ልብህ
እንደ ቀራጩ አጎነበስኩ
ምሕረት ጸጋህን ከእጅህ ለበስኩ።
ዘወትር እልል ብል ብዘምር
ስለገባኝ ነው የአንተ ፍቅር
ጌታ ምጠራው ስምህን
ለውጠኸው ነው ታሪኬን።
ዓይኖቼ አያዩም ከአንተ በቀር
የምትወደድ የምትፈቀር
ዘመድ ወገኔ ሆነኸኛል
እኔን የሚችል የት ይገኛል
Download
በSep 21, 2024 ተጭኗል