እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ሰባቱ መንጦላዕት

ሰባቱ መንጦላዕት


ሰባቱ መንጦላዕት

ሰባቱ መንጦላዕት ወዴት ተጋረዱ
ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ
ታናሹ ሙሽራ ነሽ የ15 ዓመት
ባንቺ ላይ ሲፈፀም እንግዳ ስርዓት

አዝ
አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ
ገብርዔል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ
ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበዪው
መለኮት እንዴት ነው የተዋሀደው
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል

አዝ
ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ
ከሶስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ
ስፋትና ጥበት ሰማይና ምድር
ባንቺ ተገናኙ ገባሬና ግብር
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣ

Download

በSep 21, 2024 ተጭኗል