እንኳን ደህና መጡ
ግባ
ከማህፀን እስከ ሽምግልና
ከማህፀን እስከ ሽምግልና
ከማህፀን እስከ ሽምግልና
ሚጠብቀኝ ምህረትህ ነውና
በምስጋና ወደ ቤትህ ልግባ
ልሰዋልህ የከንፈሬን መባ (2×)
በኑሮ መስመር በሕይወት ጎዳና
ዕድል ፈንታየን የምታቀና
ስፈራ በትር ስዝል ምርኩዜ
ተቀኘሁልህ ባሰብከው ጊዜ
አዝ
ዘውዴ ልበልህ መከበሪያየ
ማዕረጌ ነህ መታፈሪያየ
ስምህን ይዤ ምን ጎሎብኛል
ባንተ ስላለሁ ሁሉ ተርፎኛል
አዝ
ሳትሳቀቅም ተሸክመኸኝ
ስንት ሸለቆ ጌታ አሳለፍከኝ
አልቆምም ነበር በራሴ ጉልበት
አንተ ባትሆነኝ ጽኑ ሰገነት
አዝ
ይህ ሁሉ ክብር ይህ ሁሉ ዝና
ያላንተ ፈቃድ መች ይሆንና
ይሁን ይደረግ ጌታየ ያልከው
እኔስ ያለኝ ቃ
Download
በSep 21, 2024 ተጭኗል