እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ድንግል ሆይ

ድንግል ሆይ

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀቀለለችው
የለምና ስፍራ ለእግዶች ማረፊያ/፪/
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደሪያ
አዝ
~~~
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ
ወረደ መላእኩ ምስራች ሊያወራ
የህፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ ማይነገር/፪/
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር
አዝ
~~~
ሰባሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ እጣን ከርቤወን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ለአለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ ማይነገር/፪/
ማርያምም በልቧ ትጠብቀዉ ነበር
አዝ
~~~
የይሁዳ ምድር ምስጋናን ተሞላ
ንጉስ መቷል እና ከናዘሬት ገሊላ
ታምሩን ትናገር ቤተለሔም ታውራ
ዝማሬ ሲውጣት ተረስቶ ቆጠራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ ማይነገር/፪/
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር
አዝ
~~~
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ እደሰው
በጠባቡ ደረት ማንን እንምሰለው
ገረማት ጥበቡ ታናሿን ሙሽራ
ተዋህዷል እና ቃል ከስጋ ጋራ
ይህ ሚሰጢር ግሩም ነው/፪/
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር።

Download

በSep 21, 2024 ተጭኗል