እንኳን ደህና መጡ
ግባ
አድርገህልኛልና
አድርገህልኛልና
አድርገህልኛልና በቸርነትህ
አመሰግንሃለሁ እልል
ለዓለም/2/ አማኑኤል እገዛልሃለሁ ለዘላለም
አ.ዝ.....................//
ቀኑ ጨልሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ
ይችግር አረንቋ ፊቴ ተደቅኖ
ረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ
ፈፅሞ አራክልኝ የልቤን ትካዘዜ
አ.ዝ..............//
አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያዬ
ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻዬ
እንደማትተወኝ አሁን አውቄአለሁ
ካለኝ ነገር ሁሉ ባንተ ታምኛለሁ
አ.ዝ............//
ጥቂቷን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ
የምመልስልህ በላገኝ ስጦታ
በቀንም በለሊት ሁሌ የሚያበራ
ምንክር ለባህሪሀ እፁብ ያንተ ሥራ
አ.ዝ.................//
አምላክ ሆይ ምስጋና ላንተ ይገባሃል
ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሰጥተሃል
ድሃ ነኝ አልልም ሐብቴ አንተ ነህና
ማሰሮዬ ሞልቷል ላይጎል እንደገና
Download
በSep 21, 2024 ተጭኗል