እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

መልአከ ሰላም

መልአከ ሰላም


መልአከ ሰላም ዑራኤል
ወመልአከ ሕይወት
ወመልአከ ሕይወት አንተ

ምስጢረ ሰማይን ለሄኖክ ያስረዳህ
ጥበብን ለዕዝራ በጽዋ ያጠጣህ
/ከሳቴ ጥበብ ነህ ዑራኤል ስዩም
መራኄ ብርሃናት መልአከ ሰላም/(፪)
      አዝ= = = = =
ለድንግል ማርያም በጊዜ ስደቷ
የመንገዷ መሪ ሆነህ እረዳቷ
/የግብፅን በረሃ አብረህ ተጉዘሃል
ታማኝ አገልጋይ ነህ ክብር ይገባሃል/(፪)
       አዝ= = = = =
ከመላእክት ሁሉ የሚለይ ክብርህ
ዑራኤል ዑራኤል ብርሃን ነው ስምህ
/የጌታን ደም ቀድተህ በጽዋ ብርሃን
በደመ መለኮት ዓለምን ባርከሃል/(፪)
       አዝ= = = = =
ሰማያዊ ካህን የልዑል ባለሟል
ስለተጨነቁት ምህረት የምትለምን
/የምታረጋጋ የምህረት አማላጅ
መዝገበ ርኅራኄ የሰው ልጆች ወዳጅ/(፪)
       አዝ= = = = =
ከመ ያዝንም ዝናም ወመባርቅት በረድ
ፍሬ በረከት እንዲሰጡ ለምድር
/በራማ ከተማ ካሉት መላእክት
ተሰመይከ አንተ ሊቀ ሥልጣናት/(፪)

           

Download

በOct 04, 2024 ተጭኗል