እንኳን ደህና መጡ
ግባ
ሥላሴ ይባርኳችሁ
ሥላሴ ይባርኳችሁ
ሥላሴ ይባርኳችሁ /2/
በሥጋ ወደሙ ዛሬ ከበራችሁ
ሥላሴ ይባርኳችሁ
እመ አምላክ ትከተልህ /2/
ፈተና እንዳይገጥምህ ድንግል ትከተልህ
እመ እምላክ ትከተልህ
ሚካኤል በኑሮአችሁ /2/
አርምሞ ማስተዋል ትዕግስትን ይስጣችሁ
ሚካኤል በኑሮአችሁ
ገብርኤል ከላይ ወርዶ /2/
እርሱ ይራዳችሁ በክንፎቹ ጋርዶ
ገብርኤል ከላይ ወርዶ
ዑራኤል በምልጃው /2/
የእውቀትን ጥበብ ይስጥህ በጽዋው
ዑራኤል በምልጃው
ጊዮርጊስ አይለያችሁ /2/
በመከራ ጊዜ ጽናቱን ይስጣችሁ
ጊዮርጊስ አይለያችሁ
Download
በOct 06, 2024 ተጭኗል