እንኳን ደህና መጡ
ግባ
ይህን ላደረገ
ይህን ላደረገ
ይህን ላደረገ ሃሌሉያ በሉ
እግዚአብሔር ታማኝ ነው ሁልጊዜ በቃሉ
ሙሽራው ሙሽሪት እንኳን ደስ አላችሁ
የያዕቆብ አምላክ ሞገስ ኾነላችሁ
ስንቱን ተራራ አልፈነዋል
በሰገነት ላይ አቁሞናል
እስቲ እንዘምር በደስታ
ሁሌ ታማኝ ነው የኛ ጌታ
ከእኛ የሆነ ምንም የለም
ተመስገን ጌታ ለዘላለም
ስራህ አበራ በምስጋና
በሙሽሮች ላይ እንደገና
አዝ
የማይሆን መስሎ የታየን
በእግዚአብሔር ኾኖ ስላየን
እንደ አሳፍ ልጆች ተሰልፈን
ስሙን በቅኔ ለማመስገን
የተባረከ በመዳፉ
ቅኔን ያፈሳል ሁሌ በአፉ
ከመላእክት ጋር አንድ ኾነናል የእግዚአብሔር ሥራ መስጦናል
አዝ
ጋኑ ቢጎድል የወይን ጠጁ
ያስባል ጌታ ለወዳጁ
መናኛው ይውጣ ከቤታችን
አዲስ እንጠጣ እርሱን ይዘን
አቤንኤዘር ነው መዝሙራችን
እየረዳን ነው አምላካችን
ፊታችን በራ በደስታ
ውበት ኾኖናል የእኛ ጌታ
አዝ
ጋኑ ቢጎድል የወይን ጠጁ
ያስባል ጌታ ለወዳጁ
መናኛው ይውጣ ከቤታችን
አዲስ እንጠጣ ጌታን ይዘን
አቤንኤዘር ነው መዝሙራችን
እየረዳን ነው አምላካችን
ፊታችን በራ በደስታ
ውበት ኾኖናል የእኛ ጌታ
Download
በOct 06, 2024 ተጭኗል