እንኳን ደህና መጡ
ግባ
እናቴ እመቤቴ
እናቴ እመቤቴ
እናቴ እመቤቴ /የማጠፊው ከአፌ/(፪)
በረከቴ አንቺ ነሽ /የመስቀል ስር ትርፌ(፪)
አምላኬ ሸልሞኝ ለዘለላም ያዝኩሽ
ጌታን የማይብሽ ብሌኔ አደረኩሽ
በልቤ ላይ ይፍሰስ የፍቅርሽ ጸዳሉ
የሚጣፍጥ ስምሽ መድኃኒት ለሁሉ
ተወዳጁ ልጅሽ ጸጋዉን ያብዛልኝ
እድሜዬ እስኪፈፀም ለክብርሽ እንድቀኝ
አዝ= = = = =
ነፍሴ እንዳትጎዳ እንዳትቀር ባክና
ብርታት ሆኖልኛል የስምሽ ምስጋና
እኖራለሁ ገና ንዒ ንዒ ስልሽ
ክብሬ ነሽ ጌጤ ነሽ ከአፌ ማልነጥልሽ
አዝ= = = = =
ሲነጋም ጠራሁሽ ሲመሽም ጠራሁሽ
ስዕልሽ ፊት ቆሜ ሰዐሊ ለነ እያልኩሽ
አሜን የምልብሽ መነጋገሪያዬ
የአማኑኤል እናት አንቺ ነሽ ቋንቋዬ
አዝ= = = = =
መች በሥጋ ጥበብ ሰው ላንቺ ይቀኛል
ከአምላክ ካልተላከ ከፊትሽ ይቆማል
አንቺን ማመስገኔ አንቺን ማወደሴ
በልቡ ያሰበሽ ፈቅዶ ነው ሥላሴ
አዝ= = = = =
ብዙ ተቀብዬ ጥቂት አልዘምርም
ለእናትነት ፍቅርሽ ከቶ ዝም አልልም
እኔን በዕደ ፍቅርሽ የምትባርኪ
ኦ ምልእተ ፀጋ ድንግል ሰላም ለኪ
Download
በSep 21, 2024 ተጭኗል