እንኳን ደህና መጡ
ግባ
እግዚአብሔር መልካም ነው
እግዚአብሔር መልካም ነው
እግዚአብሔር መልካም ነው
በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው (፪)
ከገነት ሲሰደድ አዳም አባታችን
ሞት ነግሶብን ሳለ በእኛ በሁላችን
ቃል እንደገባለት ተወልዶ ሊያድነው
በመከራ ጊዜ መሸሸጊያ ሆነው (፪)
አብርሃም ከካራን ከእናት ከአባቱ ቤት
ከነአን ሊገባ ሊሰደድ በእምነት
ከተሰጠው ተሰፋ አንዳች ሳይጎልበት
እንደ ምድር አሸዋ ዘሩን አበዛለት (፪)
በኀዘን ችግር በመከራ ጊዜ
ጭንቅን የማያርቅ ነው የልብን ትካዜ
የቀደመው እባብ ሰላሜን ሲነሳኝ
እግዚአብሔር መልካም ነው ኀዘኔን አስረሳኝ(፪)
የቀደመው እባብ ሰላሜን ሲነሳኝ
ክርስቶስ ኢየሱስ ኀዘኔን አስረሳኝ
Download
በSep 21, 2024 ተጭኗል