እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

አድገናል ከደጁ

አድገናል ከደጁ



አድገናል ከደጁ ተመግበን ከጁ
አይነካንም ክፉ ገብተን ከእቅፉ

ከክብሩ ዙፋን ቤተ መቅደሱ
ስለጠበቀን ታይቶን መንፈሱ
በልዩ ሞገስ ቆመናል ዛሬ
ለረዳን መላክ ይዘን ዝማሬ
     አባታችን መልዓኩ ሚካኤል
     ምልጃህ ብርቱ ክብርህም ነው ኃያል

    አዝ=====

እየጠበቀን ቀንና ሌሊት
ከብረን ታይተናል ሆኖን በረከት
ስለወደቀ አስጨናቂያችን
አይልን ለብሰናል በታዳጊያችን
       አባታችን መልዓኩ ሚካኤል
      ምልጃህ ብርቱ ክብርህም ነው ኃያል

    አዝ=====

ስሙ ክብራችን ክንፉ ቅጥራችን
ማን እንደ እግዚአብሔር እረዳታችን
ምክሩ ለልሁል ለእያው ጌታ
ምድሪቱ ትታይ በክብር በርታ
        አባታችን መልዓኩ ሚካኤል
        ምልጃህ ብርቱ ክብርህም ነው ኃያል

    አዝ=====

ተፍቆልና የሞቴ ጦማር
አውንም ደጅ መቅደስ ልማር
ዝማሪን ባንተ ህያው ከልቤ
በብሩ ዜማ በእንባ ታጅቤ
        አባታችን መልዓኩ ሚካኤል
       ምልጃህ ብርቱ ክብርህም  ነው ኃያል

Download

በOct 13, 2024 ተጭኗል