እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ወዳጅ ነህ ለሁሉ

ወዳጅ ነህ ለሁሉ



ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ነህ ለሁሉ
ዛሬም ቆመሀል በኪዳንህ ላሉ

ክንፍህን ዘርጋ ሚካኤል ቅደም ከፊቴ
ምራኝ መንገዴን እንዳይመሽ ልድረስ ካባቴ
እንዴት ይገፋል ጎዳናው ካላንተ እርዳታ
ጥሜን ቁረጠው በበትርህ ጭንጫውን ምታው×2

አዝ=====

ተጠመጠመ ጠላቴ በእሳት ሰንሰለት
የጌታ መልአክ ሚካኤል በሰይፍ ወድቆበት
የለም ከቦታው ስመለስ አጥቼዋለው
የሚረዳኝን ተሹሞ አይቼዋለው×2

አዝ=====

ከመቃብሩ ድንጋዩን አንከባለሀል
ስለረዳኸዉ ዳንኤል እጅግ ወዶሀል
ይነዋወፃል ባህሩ አንተ ስትመጣ
እግዚአብሄር ይንገስ ዳቢሎስ መድረሻ ይጣ×2

አዝ=====

አለኝ ትዝታ በቤትህ ከልጅነቴ
ስትሳሳልኝ እያየው ፀንቷል ጉልበቴ
ልዘምር እንጂ ላመስግን ታላቁን ጌታ
አንተን የሰጠኝ ጠባቂ በቀን በማታ×2

Download

በOct 16, 2024 ተጭኗል