እንኳን ደህና መጡ

ፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት

ግባ

ፈተና ቢገጥማት

ፈተና ቢገጥማት



ፈተና ቢገጥማት(2) ቅድስት አፎምያ
ሚካኤል(2) ብላ ስትጠራ ፈጥኖ አዳናት
ከጭንቅ ከመከራ(2)

ነውና እምነቷ(2) ጽኑ ምግባሯ
ሚካኤል መጣላት(2) ተአምሩን ሊሰራ
ሚካኤል መጣላት(2) ለአፎምያ ተአምሩን ሊሰራ


ፍጡነ ረድኤት መጣላት(2) ገስግሶ(2)
እንደ ኃይልነቱ ኃይሉን አፈራርሶ(2)
በመጣበት አስኬደው መልሶ


በእምነት ለጠሩህ(2) ጸንተው በሃይማኖት
ቶሎ ይደርስልናል ፍጡነ ረድኤት(2)ሚካኤል ሊቀ መላዕክት


ታላቁ ሚካኤል(2) ተራዳሂው መላዕክ
ምህረት እንዲሰጠ(2) ለምንልን ከአምላክ(2)
ሚካኤል ሆይ ፀሎታችን ባረክ
ሚካኤል ሆይ ሃገራችን ባረክ

Download

በOct 22, 2024 ተጭኗል